Wednesday, September 25, 2013

templars

ቴምፕላሮች --THE TEMPLARS

በ1118 ዓ.ም የመስቀል ጦርነት በክርስቲያኖቹ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ወደ እየሩሳሌም የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞ ለመጠበቅ በሚል ያሸነፉት በሁጎ ደ ፓይኔ እና ጎድፈሮይ ደ ሰይንት-ኦሜር መሪነት ማህበር መሰረቱ፡፡ በእስራኤል ዘውዱን የተረከበው ባልድዊን ሁለተኛ ለማህበሩ የሰለሞን ቤተ መቅደስ በነበረበት አካባቢ ቤት ሰጣቸው ስያሜአቸውንም --የቤተ-መቅደሱ ባለሟሎች - Knights Templar-- ከዛው አገኙ፡፡ በ1128 ዓ.ም በትሮይ በተደረገው ስብሰባ ማህበሩ በሰይንት በርናንድ በተቀረፁ ደንቦች መሰረት የቤተ-መቅደሱ ባለሟሎች እራሳቸውን በድህነት፣ በድንግልናና በታዛዥነት ለመያዝ ቃለ-መሀላ ፈፅመው እውቅና ተሰጣቸው፡፡
መተዳደርያቸው ምፅዋት በሚደረግላቸው ላይ እንደመሆኑ ይህ ደግሞ እጅግ እየበዛ በመሄዱ በድህነት ለመኖር የገቡትን ቃል አስረሳቸው፣ በ12ኛው ክ/ዘመን መጨረሻም በመላው አውሮፓ የተስፋፉ እጅግ ሃያል እና ሃብታም ማህበር እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ከአረቦቹ ገዳዮቹ ጋርና ከደማስቆ ጋር በስምምነት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም የእውነት መመርያቸውንና እምነታቸውን ይከተሉ ነበር ማለት ከባድ ነው፡፡ በ13ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ በቀሳውስቱ ብቻ ሳይሆን በተራው ህዝብም ጭምር በክህደት መጠርጠር ጀመሩ፡፡ የሰው መመኘታቸው፣ ግድ የለሽነታቸው፣ ለቅንጦት ያላቸው ፍቅርና ስስታምነታቸው በግልፅ የህዝብ ትዝብት ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ ምግባራቸው ለተረትም ተርፎ፡- “መጠጣትስ እንደ ቴፕላሮች ነው” ይባል ነበር፡፡
የቴምፕላሮቹ ወዳጅ የነበረው የፈረንሳዩ ንጉስ ፊሊፔ ሌ ቤል ለጳጳስ ክለመንት አምስተኛ ጉዳዩን እንዲያጣራ መልእክ ይልክለት ነበር፤ ጳጳሱ ግን አስቀድሞ መሪያቸውን ጃኲ ደ ሞላይን ለጥያቄ ጠርቶትም ነበር፡፡ የፈረንሳዩ ንጉስ ጉዳዩን በራሱ እጅ በማድረግ ጥቅምት 13፣ 1307እ.አ.አ ቴምፕላሮችን በፈረንሳይ ማጣራትና መክሰስ እንዲጀመር አስደረገ፤ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች፡
1. በማህበሩ የአባልነት መግቢያ ስነ ስርአት ላይ መስቀሉን መሳደብ፣ ክርስቶስን መካድ እና አፀያፊ የነውር ምግባሮች ማድረጋቸው፤
2. እውነተኛው አምላክ ነው የሚሉትን ምስልን ማክበር፤
3. በቅዳሴ ግዜ ለስርአተ ቁርባኑ የሚደረገው ፀሎት ማስቀረት፤
4. ተራዎቹ አለቆች ሃጥያት የማስተሰረይ ስልጣን አለን ማለት፤
5. ጋጠወጥ የሆኑ ጥፋቶችን መፍቀድ፡፡
ለዚህ ሁሉ ክስ አለቃቸውን ጨምሮ ሁሉም የእምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህን ኑዛዜ በማሰቃየት እንዲናዘዙ ያስገደዷቸው ነው ቢባል ጳጳሱ ማሰቃያ መንገድ ሳይጠቀም ያውጣጣቸውም የተናዘዙ መኖራቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ ደግሞም የፈረንሳይ ንጉስ ማሰቃያ መንገድ ባይጠቀም የሚፈራው ንጉሱ ብቻ አይደለምና ማህበሩም ሚሥጥሩን ቢያወጡ እንደሚያሰቃያቸውና እንደሚገላቸው አባል ሲሆኑ በነበረው ስነስርአት ተነግሯቸዋልና እንደማይለቀቁ ስለሚያውቁ ካልተሰቃዩ እንዴት ሊናዘዙ ይችላሉ?
ወደ ዝርዝር ጉዳዩ ሳንገባ ንጉሱ ያናዘዛቸው መንፈሳዊ ጉዳይ ነው በሚል ጳጳሱ ንጉሱ ያሰራቸውን ሁሉንም እንዲለቅ አስደርገውታል፡፡ ሆኖም በቴምፕላሮች ላይ የሚሰማው ክስ እየበረታ በመምጣቱ ጳጳሱ መልሶ ወደ ማጣራት እንዲገባ አስገድዶታል፡፡ በዚህም መሰረት ያለ ምንም ማሰቃየት አለቃቸውን ሞላይን ጨምሮ ቴምፕላሮቹ ከላይ የተገለፁት ምግባራቸውን ተናዘዋል፡፡ ሆኖም ጳጳሱ አለቆቹና በዙርያው ያሉት ስላጠፉ በማህበሩ ላይ እርምጃ አልወስድም በማለት ማህበሩን ከማገድ ተቆጠበ፡፡ በዚህም መሰረት በህዳር 1309እ.አ.አ ማህበሩ ባጠቃላይ መመርመር ተጀመረ፡፡ በጣልያን ሁሉም ጥፋታቸውን በፈቃዳቸው አምነው ተቀብለዋል፤ በጀርመን የማሰቃያ መንገድም ተጠቅሞ ለማናዘዝ ባለመቻሉ በነፃነታቸው ተለቀዋል፤ በእንግሊዝ ንጉሱ ኤድዋርድ 2ኛ ከቅናትና ጥላቻ የመነጨ እንጂ ማህበሩ ንፁህ ነው በማለት ምንም አቤቱታ እንደማያስተናግድ እየገለፀ ከቆየ በውኋላ ጳጳሱ ቴምፕላሮችን የሚወቅስ ደብዳቤ ሲያሰራጭ ኤድዋርድም ቴምፕላሮችን መመርመር ጀመረ፤ ከሁለት ሰዎች ላይ በስተቀር ማሰቃያ መንገድ ያልተጠቀመ ሲሆን ሌሎቹ በፍቃዳቸው በመናዘዛቸው ቴምፕላሮች ከእንግሊዝም ታግደዋል፡፡
የፈረንሳዩ ንጉስና ጳጳሱ ቴምፕላሮቹን ያሳደዷቸው ሃብታቸውን ለመንጠቅ ነው ለሚባለው ክስ ታሪክ እራሱ ያስተባበለው ነው፡፡ ጳጳሱ እንደሆን የቴምፕላሮቹን ጉድ በማሳወቅ የሚጠቀመው ነገር የለም እንዲያውም ካቶሊካውያንን አንገት የሚያስደፋ በመሆኑ ውዝግቡ ሲጀመር ጀምሮ በጥንቃቄ ነበር የያዘው፡፡ ንጉሱም ቢሆን ከተወገዱ በውኋላ ከንብረታቸው አንድም አልነካም ከተወገዙ በውኋላ ንብረቶቻቸው ለእየሩሳሌሙ ቅዱስ ዮሐንስ ባለሟሎች (Knights of St. John of Jerusalem) ነው የተሰጠው፤ ሌላው ቀርቶ ፓሪስ የሚገኘው የቴምፕላሮቹ “ቤተ-መቅደስ” እስከ ፈረንሳይ አብዮት [1780ዎቹ] ግዜ ድረስ የዮሐንስ ባለሟሎች ንብረት ነበር፡፡ የንጉሱ ግምጃ ቤት ሀላፊ ፍርዱን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለማካካስ የሚገባውን አስቀርቷል፡፡
እንዲህ ማድረጉ የጳጳሱን ፈቃድ ሳያገኝ ነው የሚል ማብራርያ አሁን እናደምጣለን ግን የሞራል ጥያቄውን እንተወውና እንደ ፖሊሲ ንጉሱ እንዲህ ንብረታቸውን የማይነካ ከሆነ ለምንድን ነው የገቢ ምንጭ የነበሩትን ዜጎች በማሳደድ እራሱን የሚጠምደው፣ ትርፍ የማያገኝበት ከሆነ? በሌላ አነጋገር እንቁላል የምትጥልለትን ዶሮ ለምንድን ነው የሚያጠፋት፣ እንቁላሏን እንደማያጣ ሳያረጋግጥ? ንጉሱ ከቴምፕላሮቹ ሃብት የተጠቀመው ወይም ያገኘው ምንም የለም!
ስለዚህም ንጉሱ ቴምፕላሮቹን የተቃወመው ንብረታቸውን ተመኝቶ ነው የሚለው መከራከርያ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ቢሆን እንኳ ሊሆን የሚችለው የቴፕላሮቹ ሃብት የፈጠረው የስልጣን ተቀናቃኝነት ሊባል ይችላል፤ የቴፕላሮቹ ማህበር በኢምፓየር ውስጥ ያለ ኢምፓየር ነበር፡፡ ማህበሩ የንጉሱን ትእዛዝ ጥሶ ግብር መክፈል ትቶ ነበር፡፡ በሁሉም ከተሞች ቤቶች (ህንፃዎች) ነበሯቸው በነዚህም እንደ ዛሬዎቹ አለም አቀፍ የፋይናንስ ባንኮች ስራዎችን ይሰሩ ነበር፡፡ ላምጭው እንዲከፈለው እሚያዙ ወረቀቶችን ይሰጣሉ፣ በተቀማጭ ካፒታል ከትርፍ ክፍፍልና አመታዊ ክፍያ ይፈፅማሉ፣ ብድር ይሰጣሉ፣ የግለሰብ ሒሳቦችን ይይዛሉ፣ ላልቻሉ ባላባቶች ግብር ይሰበስባሉ፡፡ ይህ ምናልባት ከአሌክሳንድርያ አይሁዶች የተማሩት ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ ማህበረሰባውያን (ሶሻሊስቶች) ካፒታሊዝም መጥፎነት እያሉ ስለ ሞኖፖሊ የሚነግሩን በዛ ጨለማ ዘመን የመቆጣጠርያ ሕጎች ሊወጡ በማይችሉበት ዘመን ቴምፕላሮቹ ፋይናንሻል ሞኖፖሊን እውን ሊያደርጉት ተቃርበው ነበር፡፡
አንዳንድ ማሕበረሰባዊ አብዮታውያን ንጉሱ ቴምፕላሮቹን የተቃወመው ንብረታቸውን ተመኝቶ ነው ይሉናል፣ በፈረንሳይ አብዮት (የሌሎቹንም ሃገራት ጨምሮ) አብዮተኞቹ የባላባቶቹን ንብረት ሲወርሱ ግን ከቅናት ተነሳስተው ነው ብለው አይፅፉም፡፡ በዚህም ምክንያት በአለማችን ታሪክ የቅናት ሰለባ የሆኑ ሃብታሞች ወይም ካፒታሊስቶች እና ሃብት በማከማቸት በማህበረሰባውያን ከመወገዝ የተረፉት ቴምፕላሮች ብቻ ያደርጋቸዋል፣ ከአይሁዶች ውጪ (እነዚም በማሕበረሰባውያን አይነቀፉም፡፡) ቴምፕላሮች ከመወገዝ ነፃ የሆኑት የንጉሱ ጠላት ስለሆኑ ነው? ወይስ የዓለም አብዮት አራማጆች የግል ንብረት ባለቤትነትን ሲቃወሙ፣ ዓለም አቀፋዊ ፋይናንስን በተለይ ከፀረ-ክርስቲያን አቋም ጋር ሲጣመር ተቃውመው ስለማያውቁ ነው?
ቴምፕላሮች ለሃይማኖታቸው የገቡትን ቃል አልጠበቁም፣ በድህነት መኖር ቀርቶ ሃብት ማካበታቸው ብቻ ሳይሆን በትእቢትም ታብየዋል፣ የድንግልና ቃል ገብተው ግብረገብ ረስተዋል፡፡
ከረዥም ግዜ በውኋላ ስለ ቴምፕላሮች ትክክለኛውን ማስረጃ ማግኘት የሚከብድ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን ቴምፕላሮች ጥፋተኛም ንፁሃንም ነበሩ፡፡ ገሚሶቹ የሚስጥር ዶክትሪኑን እንዲያውቁ የሚደረግ ሲሆን አብዛኞቹ ግን ሚስጥሩን ሳያውቁ መጠቀምያ ነበር የሚደረጉት፡፡ ይህም የሚረጋገጠው አንዳንድ አባሎች ስቃይ ቢበዛባቸውም እንኳን የተናዘዙት ጥፋተኛነት አለመኖሩ ነው፡፡ ከኢስማኢላውያን ጀምሮ ያለ የሁሉም የሚስጥር ማህበራት ስልት ነው፡፡
የቴምፕላሮች የክህደት ትምህርት እንግዲህ እንደሚከተለው ነው፡- መልካም አምላክ እና ክፉ አምላክ የሚለው የጥንዳውያን ዶክትሪን ነው፡፡ መልካሙ አምላክ መግለፅ አይቻልም እናም እርሱን የሚወክል ምልክት የለም፤ ክፉውን አምላክ ለመወከል የሚያስፈራ ፊት ያለው ምስል ይቀርፁለታል፡፡ የቴምፕላሮች አምልኮም ለክፉው አምልክ ነው፡- እሱ ነውና በምድር ላይ ብልፅግና የሚሰጠው፡፡ ሉሲፈራውያን ሴጣን አምላኪዎቹ እንደሚሉት፡- የፈጣሪ የመጀመርያ ልጅ የሆነው ሳጥናኤል ወይም ሉሲፈር ብቻ ነው በሙታን ላይ ስልጣን ያለው፣ ክርስቶስ ታናሽ ወንድሙ ይህ ስልጣን የለውም ይላሉ፡፡ ይህ አዲስ ሳይሆን ከካባላ ጀምሮ የነበረ የክህደት ትምህርት ነው፡፡ የማህበሩ አባል የሆነው ሎይዝሉ (Loiseleur) በኑዛዜው እንዳስረዳው የሚያመልኩት ምስል ባፎሜት (Baphomet) ነበር የሚሉት፡፡ ሌሎች ብዙ መላምቶችም አንደኛው የጥንታዊ የአምላክ አምልኮ ተከታዮች ናቸው የሚለው ነው፡፡ መስራቻቸው ሁጎ ደ ፓይኔ በ1118 ቴምፕላሮችን ሲመሰርት እስራኤል የነበረው የጥንታዊ አምልኮ አባት ቲኦስሌት (Sovereign Pontiff and Patriarch, Theoclet) ከሚስጥሩ አካፍሎታል ይባላል፣ ቴምፕላሮቹም የጴጥሮስን እምነት ትተው የዮሐንስ ተከታይ ሆኑ ይባላል፡፡ [በነሱ የፈጠራ ታሪክ መሰረት ማለት ነው፡፡]
የጥንታዊ አምልኮ ታሪክ እንዲህ ነው፡- ከግብፅ ሚስጥራት ሙሴ ከተካፈለ በውኋላ አጋሮቹን ነፃ ለማውጣት ተጠቀመበት እውቀቱም በአፍ ሲተላለፍ ነበር፤ ክርስቶስም እንዲሁ ሚስጥራቱን ሁሉ ያወቀ ነው፣ እርሱም ለሃዋርያቱ አካፈላቸው ይላሉ፡፡ ይህ የተለመደው ክርስትናን የማጣመም ፈጠራ ነው፡፡
የቴምፕላር አባል ለሚሆኑት የሚነገራቸው ታሪክ አይሁዶቹ እየሱስን ለማሳነስ የፃፉት፣ መጀመርያ አካባቢ ያየነው “ቶሌዶት የሹ” የተባለው መፃህፋቸው ላይ ያለው ክርስቶስ ሃሰተኛ ነብይ ነበር የሚለው ታሪክ ነው፣ አንድ የካታሎኝ ጋልሴራንደስ ደ ቱ (Galcerandus de Teus) የተባለ ቴምፕላር እንደተናዘዘው ከሆነ ቴምፕላሮቹ ሲፀልዩ፡- “ “ፈጣሪን ማርያም መግደላዊትንና በመስቀሉ ላይ ያለውን ወንበዴ እንደማረ እንዲምረኝ” ብለን ነው፡፡ መስቀሉ ላይ ያለው ወንበዴ ስንል ምህረት ያገኘው በቀኝ የተሰቀለው ሳይሆን ክርስቶስ እራሱን ነው፣ ጌታ ሳይሆን ነኝ በማለቱ የአይሁዶች ንጉስ ሳይሆን ነኝ በማለቱ፡፡ መጨረሻም ከመሞቱ ከጥቂት ግዜ በፊት ጎኑን በወታደሩ ሲወጋ ተፀፅቶ ባሰማው ጥሪ እውነተኛው አምላክ ይቅር ብሎታል በማለት፡፡” ቃል ሰቷል፡፡
ሌሎችም ብዙ ጥርጣሬዎች አሉ ለዚህች አጭር ፅሁፍ ይህ ይበቃል፡፡ እነዚህና ሌሎችም የማጣመም ስልቶች እስከዛሬ ድረስ በተለያዩ ዘዴዎች የሚተገበሩ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment