Wednesday, September 25, 2013

ፍሪሜሶኖች -- FREEMASONS

ፍሪሜሶኖች -- FREEMASONS

ፍሪ ሜሶን በርግጠኝነት በመቶዎች ዓመታት በሚያከራክር ሁኔታ ደሞ በሺህ አመታትየሚቆጠር እድሜ ያለው የሚስጥር ማህበር ነው፡፡ ፍሪሜሶናዊነት እራሱን እንደ በጎ አድራጎትድርጅት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህ እውነት የሚመስለው ከሚመለምላቸው ሰዎች 97 መቶኛየሚሆኑት ሰመያዊ መዓርግ” ከሚባሉት ከመጀመርያዎቹ ሶስት መዓርጎች ስር የሚገኙትገራገሮች ባላቸው ግብረገብና ከማህበረሰቡ የተሻሉ ግለሰቦች ቀናነት የሚታይ በመሆኑ እውነት ሊያስመስለው ይችላል፡፡ እውነቱ ግን ከፍ ያሉት መዓርጎች በፍሪሜሶን መክብብ ውስጥ ኮር(ማህልቦታውን የያዙ ጥቂቶች ለዓለም አቀፋዊ የበላይነት ግባቸው በመሳርያነት ነውየሚያውሉት፡፡ በራሳቸው አንደበት፡-


ፍሪሜሶናዊነት በጥምረት ውስት ያለ ጥምረት ነው ከውስጥ ያሉ የተመረጡትወንድማማችነትን የሚከልል ውጫው ድርጅት ነው፡፡… እንዲህ የተለያዩ ግንየሚደጋገፉ ማህበራትን መመስረት የግዴታ ነው፣ አንዱ የሚታይ ሌላኛው የማይታይ፡፡የሚታየው ማህበር አባሎች እራሳቸውን ለግብረገብ፣ ለእውቀት፣ ለጥምረት፣ለአርበኝነት እና ለሰብአዊነት ጉዳዮች የሚያውሉ ናቸው፡፡ የማይታየው ማህበር እጅግሚስጥራዊና የተከበረ/የተፈራ ጥምረት ነው፣ አባሎቹም እራሳቸውን ውስብስብ /ሚስጥራዊ ለሆነው አርካኑም አርካንድረም [ቅዱስ ሚስጥርየሚያውሉ ናቸው፡፡ እኚህ ስለማህበራቸው ለመፃፍ የሞከሩ ወንድሞች በፅሁፎቻቸው ይህ ሚስጥራዊ የሆነውንለፍሪሜሶን አካል፣ ልብ ለሰው አካል እንደሆነ የሚመስለውን የእውነት ሚስጥራዊየሆነው የውስጣዊ ማህበሩን አያካትቱትም፡፡ ለዚህ ስራ በእያንዳንድ ትውልድ እጅግጥቂቶች ናቸው የሚመረጡት፡፡ እኚህ ታላቆቹ ከሚስጥሩ የተቋደሱ የፍሪሜሶንፈላስፎች የእያንዳንዱ ስነመለኮታዊና አመክንዮታዊ ተቋም መሰረት የሚያውቁ /ሊቃውንትናቸው፡፡” ማንሊ ሃል 33 መኣርግ የደረሰ ፍሪሜሶን “Lectures on Ancient Philosophy” ላይ እንደፃፈው፡፡
ይህ ፀሃፊያቸው እንደሚመሰክረው የሚስጥር ቀኖና አላቸው፤ እራሳቸውን ደሞ እንደሁሉን እምነቶችና ፍልስፍናዎች መሰረት አዋቂ ሊቃውንት አድርገው ይቆጥራሉ፡፡
ከምንም በላይ ፍሪሜሶኖች ከማንም በላይ ስለ ታሪካቸው ወይም አጀማመራቸው ሊያቁ ይገባ ነበር ሆኖም ግን የሜሶን ምሁራን በዚህ ዙርያ አንድ አቋም የላቸውም፤ ዝቅተኛ አባሎቻቸውም ለዚህ ዴንታ የላቸውም፡፡
የሮያል ሜሶናዊ ሳይክሎፖድያ (Royal Masonic Cyclopodia) [የራሳቸው የሜሶኖች ህትመትእንደሚያስቀምጠው ከሆነ ስለ ሜሶን ማህበር አጀማመር ከአስራ ሁለት ያላነሱ ሃሳቦችን ይዘረዝራል፡፡ ይህ ግን አሳሳች ነው ምክንያቱም የሜሶን ምንጩ ከአስራ ሁለቱ አንዱ ነው የሚል ሃሳብ ስለሚሰጥ፡፡ ሆኖም ግን የሜሶኖችን ምንጭ በአጠቃላይ በሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን፡-
1.      የሥራ ሜሶኖች እና፤  
2.      የመላምት ሜሶኖች፡፡
1. የሥራ ሜሶኖች -- OPERATIVE MASONRY
እኚህ ሜሶኖች በግንባታ ጥበብ የተሰማሩ ጠቢባን ማህበር ሲሆን አንዳንዶች ምንጫቸውን በትክክለኛ ማስረጃ ማረጋገጥ ባይችሉም በሺህ አመታት እንደሚቆጠር ይናገራሉ፡፡ ስለህልውናቸው መናገር የሚቻለው በ926 ዓ.ም የዮርክ ቻርተር በማጣቀስ ነው ይህም ሰነድ ቢሆን ግን እለቱ አወዛጋቢ ነው፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው በመካከለኛው ዘመን በነገስታቱ እውቅና ሲሰጣቸው ጀምሮ ነው፡፡ ባጭር ግዜ ውስጥ ሚስጥራዊነታቸው ጥርጣሬን ማስጫር ጀመረ ንጉስ ሄነሪ ስድስተኛ በፓርላማ ውሳኔ ሜሶኖችን አሳግዶ ነበር፣ ንግስት ኤልሳቤት በዮርክ ሲያካሂዱ የነበረውን አመታዊ ስብሰባቸውን ለመበተን ሰራዊት ልካ ነበር፡፡
ይህ ጥርጣሬ ሚስጥራዊነታቸው የቀሰቀሰው ቢሆንም ከሙያቸው ውጪ ሌላ ነገርም እንደሚያከናውኑ የፃፉ አሉ፤ ደንቦቻቸው ግን ለህግና ለአለቆቻቸው ተገዢ እንዲሆን የሚያዝ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከግንባታ ሙያ ውጪ ሌሎች ሚስጥራት እንደነበሯቸው የሚጠረጠረው ጠባቂ ከሚያደርጓቸው የማህበሮቻቸው መሪ ባላባቶች ውጪ ሌሎች ከግንባታ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ግለሰቦች በአባልነት መያዝ መጀመራቸው ነው፡፡ በጥቅምት 16፣ 1646 ዓ.ም ኤልያስ አሽሞል (Elias Ashmole) የተሰኘ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር የፍሪሜሶን አባል እንደሆነ በማስታወሻው አስፍሮ ይገኛል፡፡ እሱና የዘረዘራቸው ሰዎች ከሙያው ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ቢያንስ ከዚህ ግዜ ጀምሮ ፍሪሜሶናዊነት ከግንባታ ጋር ብቻ የተገናኘ አለመሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በ1703ዓ.ም የሰይንት ፖል ቤት (ሎጅ) በኦፊሻል ሜሶናዊነት ከግንበኞች ውጪ ሌሎችንም መቀበል እንደሚችል አሳወቁ፡፡ እስከዚህ ግዜ ድረስ በሜሶናዊነት የበላይ ቦታ የያዙት ግንበኞቹ (አርክቴክቸሮቹ) ነበሩ፡፡ በ1717 ግን ግራንድ ሎጅ (ዋና ቤት) ሲቋቋም ግንበኞቹ ቦታቸውን ተነጠቁ፡፡ ከዚህ በውኋላ አሁን የምናውቀውን የሜሶን የመሰለ በአሎች፣ ደንቦች እና ህጎችን ይዞ እንደ አዲስ ተቋቋመ፡፡
2. መላምት ሜሶኖች --SPECULATIVE MASONRY
የሜሶኖች ፍልስፍና ወይም አምልኮ የያዘው “የመላምት ሜሶናዊነት” መቼ እንደተጀመረ ማስረጃ የሌላቸው አወዛጋቢ ታሪኮች አሉ ሆኖም እንደ ከዚህ በፊቶቹ የሚስጥር ማህበራት የተቀራረቡ ትረካዎች ናቸው፡፡ በሰፊው ማየት ባያስፈልግም የሜሶኖች ፅሁፎች እንደሚያሳዩት ወደ አይሁዶቹ ካባላ የቀረበ ስርአት ያላቸው ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ የሚጠቅሱትና ዝነኛ አፈ ታሪካቸውን ግን መመልከት ይኖርብናል፡፡
ሰለሞን ቤተ መቅደሱን በሚሰራበት ግዜ ኪራም የናፍታሊ ጎሳ ሰው የጋለሞታ ልጅ የሆነ ግንበኛ የጢሮስ ንጉስ የሆነው ኪራም ለሰለሞን ይልክለታል፡፡ እስከዚህ ድረስ በመጽሐፈ ነገስት እንደሚገኘው ነው ከዚህ በውኋላ ግን ሜሶኖች አፈ ታሪካቸውን ይጨምራሉ፡- ቤተ መቅደሱ በሚሰራበት ወቅት ስርአት ለማስያዝ እንዲመች ሰራተኞቹ በሶስት መአርጎች የተከፋፈሉ ነበሩ፡፡ ጀማሪ፣ አጋር ሙያተኛ እና የጠራብያን አለቃ (Entered Apprentices, Fellow Crafts, and Master Masons) ተብለው፡፡ የመጀመርያ ሁለቱ በተለያዩ የይለፍ ቃላቶች እና እጅ አጨባበጦች መለየት ይቻላል በዚህም መሰረት ደሞዛቸው ይከፈላቸዋል፡፡ ሦስተኛው መአርግ ላይ ግን ሦስት ሰዎች ብቻ ነበሩ፡- የጢሮስ ንጉስ ኪራም፣ ኪራም የጋለሞታይቱ ልጅ እና ሰለሞን፡፡
አጋር ሙያተኛ የነበሩ ሰዎች ሚስጥሩን ለማወቅ አሲረው ኪራም የጋለሞታይቱን ልጅ[ሜሶኖች ኪራም አቢፍ --Hiram Abiff ይሉታል] ጠብቀው በማፈን እንዲነግራቸው ቢያስገድዱትም ስላልነገራቸው ቀጥቅጠው ገለው አርቀው ቀበሩት፡፡ ሰለሞንም ሲጠፋበት ፈላጊዎች አሰማርቶ የተቀበረበትን አገኘው፣ ከተቀበረበትም አስነሳው፡፡ ይህ ታሪክ ሙሉ ፈጠራ ነው ኪራም አቢፍ የሚባል ሰው እራሱ በሂወት ለመኖሩ እንኳ ምንም ማስረጃ የለም፣ ይሄ ከሌሎች አምልኮዎች አፈ ታሪክ የተቀዳ ፈጠራ ነው፡፡ ፍሪሜሶን ከሁሉም የሚስጥር ማህበራት የተቀላቀለ ሚስጥራትን የያዘ ይመስላል ምልክቶቹም ይህን ያሳያሉ፣ ከቴምፕላሮች ጋር ያለው ትስስርም ሰፊ ነው፡፡
እንደ ቴምፕላሮቹ የማያወዛግበው ፍሪሜሶኖች ከሮዚክሩሻውያን ጋር ያላቸው ትስስር ነው፡፡ ከላይ ያየነው ኤልያስ አሽሞል አክራሪ ሮዚክሩሻዊ የነበረ ሲሆን እንዳየነው የፍሪሜሶን አባልም ሁኗል፡፡ ፍራንሲስ ቤኮን (Francis Bacon) [ብዙዎች ንግስት ኤልሳቤት ከደጅ የወለደችው እና እውነተኛው ዊልያም ሼክስፒየር እሱ ነው ይሉታል፡፡] “ኒው አትላንቲስ” የሚለው መፅሐፉ ከሚስጥር ማህበራቱ ጋር ያለውን ትውውቅ ያሳያል፡፡ እንግዲህ የ1717 የሜሶኖች ለውጥ ምንጩ እንዲህ ከመሰሉት ሮዚክሩሻውያን ተፅእኖ የወለደው ነው፡፡
አሁን ፍሪሜሶን ብለን የምናውቀው ማህበር መሰረቱ ከአንድ ምንጭ ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ስንጀምር የጠቀስነው የሜሶኖች ፅሁፍ የሚያስቀምጣቸው አስራ ሁለት ንድፈ ሃሳቦች ቅልቅል ውጤት ነው፡፡ እስካሁን የሚስጥር ማህበራቱ በሚለው መደብ ውስጥ ያለው ታሪክ በዋናነት ዋቢ የሆነችው የራሳቸውን ፅሁፎች አጣቅሳ ጥልቅና ረዥም ስራ ከሰራችው ኔስታ ዌብስተር (Nesta Webster) ነች፡፡ Secrete Societies and Subversive Movements, World Revolution, French Revolution የመሳሰሉት የተዋጣለቸው መጽሐፍቶቿ ክብርና ተደናቂነትን ያተረፉላት ስራዎቿ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment